የቁም ነገር መጥሄት ባልደረቦች ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የሄደባቸውን መንገዶች እንዲሁም ያወጣቸውን ተከታታይነት ያላቸውን ሪፖርቶች መርምረው ዶ/ር ዳንኤልንና የሚመሩትን ኮሚሽን በዓመቱ ሃላፊነቱን በአግባቡ የተወጣ የመንግስት መስሪያ ቤት ብለዋቸዋል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው
ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሥር መንስኤ የሆኑ የተጠያቂነት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት መላላት እና የሰላም እና ደኅንነት እጦት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የመንግሥት ከፍተኛ እና ያልተቋረጠ ጥረት ያሻል (የ2015 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት)
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ይህ ሪፖርት ኮሚሽኑ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የከተማ ጽሕፈት ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በጥቅሉ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በለያቸውና በሚሠራባቸው የትኩረት ዘርፎች (Thematic Areas) ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን በሪፖርቱ...
ይህ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፓርት ከሰኔ 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን፣ በልዩ ልዩ የኢሰመኮ የሥራ ዘርፎች እና ጽ/ቤቶች አማካኝነት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ባለፉት አሥራ አንድ  ወራት የነበረውን ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚዳስስ ነው፡፡ ሪፖርቱ ኢሰመኮ በሚንቀሳቀስባቸው የሥራ ዘርፎች የተስተዋሉቁልፍ እመርታዎችን እና  ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም አንኳር ምክረ-ሐሳቦችን...
በተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሱ ናቸው ለተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈጻሚውን አካል እንዲጠይቅና እንዲያሳስብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቀረበ
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ባቀረቡት ሪፖርት፣ በአማራ ክልል እየተከናወነ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እስካሁን ድረስ በንፁኃን ሰዎች ላይ የሞት፣ የመቁሰል፣ የሀብት ውድመትና የመፈናቀል ጉዳት ከመድረሱም በላይ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ተናግረዋል
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) 2021/2022 Activity Report  
በጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደው ይህ ሕዝበ ውሳኔ ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው 186 ጣቢያዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች (minor electoral irregularities) ውጪ፤ አጠቃላይ ምርጫው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ነጻ የነበረ ነው
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት፣ ሕዝበ ውሳኔ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገዱበት እና ዜጎች በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንደኛው ሂደት መሆኑን ገልፀዋል