በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች፥ በቂ፣ ተደራሽ እና ወቅቱን የጠበቀ የምግብ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሶማሌ ክልል የቆሎጂ መጠለያ ማዕከል ውስጥ በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት፣ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ አስታውቋል
በሶማሊ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ምክንያት በአካባቢው የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው አሳሳቢ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል
በሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ላይ በክልሎቹ የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ተገቢ የሆነ ምርመራ በማድረግ ለተጎጂዎች ዘላቂ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል ሲል ኢሰመኮ አሳቧል
In accordance with the Kampala Convention, government security forces must refrain from acts that jeopardize the safety and security of IDP camps
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ‹‹በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልል የፀጥታ ሀይሎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን›› መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣውና ለአሻም በላከላት መግለጫ አመልክቷል
በተኩስ ልውውጡ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች በቆሎጂ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ እንደነበሩ ኮሚሽኑ ገልጿል
በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 6 ሰዎች መገደላቸወን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ
በካምፓላ ስምምነት መሠረት የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን የመጠለያ ጣቢያዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ተግባራት ሊቆጠቡ ይገባል