በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ከፍትሕ ተቋማት ሥራዎች ባሻገር ማኅበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ ትልቅ ሚና አለው
በኢትዮጵያም አረጋውያን ለመሰል የመብት ጥሰት ይጋለጣሉ የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተቋማት በአረጋውያን ዙሪያ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ ምልከታ አደርጋለሁ ብሏል
አረጋውያን እነማን ናቸው? በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ምን ማለት ነው? አረጋውያን ላይ የሚደርሱ የጥቃት አይነቶች ምን ምን ናቸው?
An elderly blind woman Older persons have the right to be protected from abuse and harmful traditional practice
An elderly blind woman አረጋውያን ከጥቃት እና ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅ መብት አላቸው
ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ያለው አረጋውያን ፍላጎታቸውን እና ሁኔታቸውን ያገናዘበ የሕግ እና የፖሊሲ ማእቀፍ በመዘርጋት ሰብአዊ መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙ ማስቻል አስፈላጊ ነው
ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት የአካል ጉዳተኞችን እና የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች እንዲያስከብርና ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟላ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል
ማእከላቱ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መመዘኛዎች፣ የተ.መ.ድ. የአረጋውያን መርሆችና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣውን አነስተኛ መስፈርት በማሟላት የአገልግሎቶቻቸውን ጥራት ለማሻሻል እና ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ መንግሥት ድጋፍ በማድረግ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል
አባል ሀገራት አረጋውያን በሁሉም ጊዜ ሰብአዊ እንክብካቤ፣ ጥበቃ እና ክብር እንዲያገኙ የማድረግ እና የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዳይነፈጋቸው የማድረግ ግዴታ አለባቸው