ወጣቶች፣ ታዳጊዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ዘርፍ ባለሞያዎች በውድድሩ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል
በተለያዩ የፊልም እና የኪነጥበብ ባለሞያዎች እገዛና ትብብር የሚዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል፣ በሰዎች የዕለት ተለት ሕይወት ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የሰብአዊ መብቶች ዙርያ የሚያጠነጥኑ አጫጭር ወይም ሙሉ (ፊቸር ፊልሞች)፣ ዘገባዎች ወይም ልብወለድ ይዘት ያላቸው ፊልሞች የሚታዩበት፣ ተመልካቾች ፊልሞቹን ካዘጋጁ ባለሞያዎች ጋር ወይም ከተዋንያን ጋር የሚወያዩበት፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን የሰብአዊ መብቶች ሥራዎች የሚደግፉ አጋር ድርጅቶች እና ባለሞያዎች የሚሳተፉበት መድረክ ነው
በቂ የመኖሪያ ቤት የማግኘት እና በሕይወት የመኖር መብት ላይ ያተኮረው ሦስተኞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የፊልም ፌስቲቫል "ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቶቹ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ ሆነው እንዲቀርቡ ጥሪ ቀረበ
ሕይወት፣ ትርጉም ያለው ሕይወት፣ ምንድን ነው? የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ ወይም የተፈናቃይ ወይም የአረጋዊ ሕይወት ምን ይመስላል?
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል በእ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 10 የሚውለውን ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን የሚያስብ ነው
በ2016 ዓ.ም. በኅዳር 30 ቀን የሚውለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን (December 10) የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል
የ2016 ዓ.ም. የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ኅዳር 30 ቀን የሚውለው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት ዝግጅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፤ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል