በተለያዩ አካባቢዎች ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መልሰው ስላልተቋቋሙ በተራዘመ የመፈናቀል አውድ ውስጥ ዓመታትን ለማሳለፍ ተገደዋል
የመንግስት አገልግሎት የተቋረጠባቸው ስላሉ የተቸገሩ ነዋሪዎችም መኖራቸው በመጥቀስ የተጠቀሱትና ተያያዥ ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጣቸው የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል
በአዲስ መልኩ በሚዋቀሩ አካባቢዎች የሚነሱ የደመወዝ እና ተያያዥ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት በጤና እና በትምህርት መብት እንዲሁም በአካባቢዎቹ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሉ ሥጋቶችን ይቀርፋል
የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው
ከሰብአዊ መብቶች አኳያ ሊቀጥሉ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መልካም አሠራሮች ቢኖሩም የአረጋውያን መንከባከቢያ ማእከላቱ በአብዛኛው ቋሚ የገቢ ምንጭ የሌላቸው እና በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ውስን መሆኑ አገልግሎታቸውን ለማስቀጠልና ዘላቂነቱን (sustainability) ለማረጋገጥ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል
በጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የተካሄደው ይህ ሕዝበ ውሳኔ ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው 186 ጣቢያዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች (minor electoral irregularities) ውጪ፤ አጠቃላይ ምርጫው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ነጻ የነበረ ነው
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት፣ ሕዝበ ውሳኔ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገዱበት እና ዜጎች በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንደኛው ሂደት መሆኑን ገልፀዋል
ምርጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመው የሕግ ጥሰት እስኪጣራ ድረስ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ እንዲቋረጥ ተወስኗል
ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች የተስተዋሉ በጎ ጅማሮች እንዲቀጥሉና ኮሚሽኑ ለእርምት እና ለማስተካከያ ያቀራባቸው ምክረ ሃሳቦች እንዲተገበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል