ማንኛውም ሰው ብቻውንም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር የንብረት ባለቤት የመሆን መብት አለው
Everyone has the right to own property alone as well as in association with others
ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው
Every human being has the inherent right to life
Victims (Families of any person who has been subjected to enforced disappearance) have the right to know the truth regarding the circumstances of the enforced disappearance, the progress and results of the investigation, and the fate of the disappeared person
ማናቸውም አስገድዶ መሰወር የተፈጸመበት ሰው ቤተሰቦች (ሌሎች ተጎጂዎች) አስገድዶ መሰወር የተፈጸመበትን ሁኔታ፣ ምርመራው ያለበትን ደረጃ እና ያስገኘውን ውጤት፣ እንዲሁም የተሰወረውን ሰው እጣፋንታ በተመለከተ እውነቱን የማወቅ መብት አላቸው
Freedom of the press and other mass media and freedom of artistic creativity is guaranteed
የፕሬስ ነጻነት በተለይም የቅድመ ምርመራ በማናቸውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን እና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብቶችን ያጠቃልላል
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት፣ ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀናት፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው
Workers have the right to reasonable limitation of working hours, rest, leisure, periodic leaves with pay