Skip to content
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Human Rights Monitoring and Investigation
        • Women’s and Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች እና ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ

June 30, 2022October 6, 2022 Event Update

የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበርን በሚመለከት በኢሰመኮ የተደረገ የክትትል ሥራ የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን የማግኘት፣ የእኩልነትና ከአድልዎ ነፃ የመሆን እንዲሁም የሥራ ዋስትና የማግኘት መብቶች እየተጣሱ እንደሆነ ማመላከቱ ተገልጾ በምክረ ሃሳቦች ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰብስቧል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ‘የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች እና ሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ የሠራተኛ ማኅበራት አባላት፣ የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንዲሁም የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ተወካዮች በተገኙበት ባሳለፍነው አርብ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡

የውይይት መድረኩ ላይ የኢሰመኮ የሲቪል፣ ፖለቲካዊ እና የማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሀገሪቱ የሠራተኞች መብቶችን በሚመለከት በሕገ-መንግሥቱ ካሉ ጉዳዩን ከሚመለከቱ ድንጋጌዎች በተጨማሪ የኢኮኖሚያዊ፣ የማኅበራዊና ባሕላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አግባብነት ያላቸው የዓለም ሥራ ድርጅት ስምምነቶችን እና የመሳሰሉ የተለያዩ የሠራተኞች መብቶችን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ተቀብላ ማፅደቋን በማብራራት ጀምረዋል። በመሆኑም “መንግሥት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በእነዚህና መሰል ድንጋጌዎች ውስጥ ለተዘረዘሩ መብቶች መከበር መሥራት አለባቸው” ሲሉ ጠቁመዋል፡፡ ዶ/ር አብዲ አክለውም መድረኩ የተዘጋጀው ሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የሠራተኞች የመብት ሁኔታ በምን መልኩ ለማሻሻል እንዲሁም አሁን ያሉ የመብቶች ጥሰቶችን በምን መልኩ ለማስቆም እንደሚቻል ግብዓት ለመሰብሰብ እና ለመመካከር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በስብሰባው በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውንና የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶችን በተመለከተ ያለውን የሕግ ማዕቀፍ የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ባለሙያ ገልጻ ያደረጉ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተሳታፊዎች በሠራተኞች ላይ የሚስተዋለው ስለ ሕጎቹ እና ስለመብቶቻችው ያለው የመረጃ እና የፋይናንስ አቅም ማነስ የሕጎቹ አፈጻጸም ላይ እክል ሲፈጥር እንደሚታይ ጠቁመዋል፡፡

የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበርን በሚመለከት በኢሰመኮ የተደረገ የክትትል ሪፖርት ግኝቶች እና የተሰጡ ምክረ-ሃሳቦችም በምክክር መድረኩ ቀርበዋል፡፡ የክትትሉ ግኝቶች የኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች በተለይም ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን የማግኘት፣ የእኩልነትና ከአድልዎ ነፃ የመሆን እንዲሁም የሥራ ዋስትና የማግኘት መብቶች እየተጣሱ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

እነዚህ ጉዳዮች ላይ በመመርኮዝ ተሳታፊዎች የቡድን ውይይት በማድረግ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል፣ ከሚወክሏቸው ተቋማት በኩልም ችግሮቹን ከመቅረፍ አንጻር ምን እንደሚጠበቅ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የኢሰመኮ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ ጉዳዩ ሁሉንም ባለድርሻዎች የሚመለከት መሆኑን በመግለጽ ውይይቱ ተገቢውን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንጻር መልካም ጅማሮ እንደሆነና ከባለድርሻ አካላቱ ጋር የሚኖረው ሥራ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል፡፡

Location Addis Ababa

Related posts

February 15, 2022August 28, 2023 EHRC Quote
ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የተወካዮች ም/ቤት ማፅደቁን ተከትሎ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ
March 24, 2022August 28, 2023 EHRC on the News
በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ግድያ ላይ የተጀመረው የእርቅ ሂደት “ተጠያቂነትን ሊያደናቅፍ” እንደማይገባ ኢሰመኮ አሳሰበ – Ethiopia Insider
June 2, 2021August 28, 2023 EHRC on the News
Ethiopia’s human rights chief as war rages in Tigray: ‘we get accused by all ethnic groups’ - The Guardian
April 21, 2021February 11, 2023 Press Release
በቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከማሺ ዞን ግድያዎች እና የንብረት ውድመት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on TwitterYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on Linkedin

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
 

Loading Comments...
 

    Search
    Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.