Skip to content
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Human Rights Monitoring and Investigation
        • Women’s and Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

መንግሥት የስደተኞችን የደኅንነት መብት መከበሩን በሚያረጋግጥበት ሂደት ለልዩ ፍላጎት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል

June 23, 2022October 6, 2022 Public Statement

የስደተኛ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ፍላጎቶቻቸውን መሰረት ያደረገ እገዛ አስፈላጊ ነው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ከታኅሣሥ ወር 1993 ዓ.ም. ጀምሮ በዓለም እና ሀገር አቀፍ ደረጃ የስደተኞችን ሰብአዊ መብቶችና ፍላጎቶች ለማሳካት የሚያስችል የፖለቲካ ቁርጠኝነትን እና የሃብት ምደባ ለማጠናከርና ለማነቃቃት በየዓመቱ ሰኔ 13 ቀን ታስቦ ይውላላል። የዘንድሮ የስደተኞች ቀን የሚከበረው ‘ደኅንነትን መሻት ሰብአዊ መብት ነው’ በሚል መሪ ቃል ሲሆን፣ ‘የደኅንነትን መብት’ ማክበር እና መከበሩን ማረጋገጥ ስደተኞች ጥገኝነት በሚጠይቁበት ሂደትም ሆነ የስደተኝነት እውቅና አግኝተው በሚኖሩበት ወቅት በእኩልነት መስተናገዳቸውን፣ ሰብአዊ ክብራቸው እና ደኅንነታቸውን መጠበቁን ማረጋገጥ ያጠቃልላል። ይህንን ቀን መታሰቢያ በማድረግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኢትዮጵያ ለስደተኞች እና ለጥገኝነት ጠያቂዎች በሮቿን ክፍት በማድረጓና ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞችን ማስተናገዷ በአወንታዊ ጎኑ የሚታይ መሆኑን አስታውሶ፣ በመንግሥት የስደተኝነት እውቅና የመስጠት ሂደትን ጨምሮ፣ ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ልዩ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ጥሪ ያቀርባል።

በኢትዮጵያ ከሚኖሩት ስደተኞች ውስጥ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ከ50% በላይ የሚሆኑት ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በ2011 ዓ.ም. በወጣው የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2011 አንቀጽ 38 ለእነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች መንግሥት ልዩ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ እገዛ እንደሚያደርግ የተገለጸ ቢሆንም፣ አተገባበሩ በርካታ ውስንነቶች አሉበት። 

ኢሰመኮ በጋምቤላ እና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 10 የስደተኛ መጠለያ ካምፖች እና መቀበያ ጣቢያ ላይ ባከናወነው የሰብአዊ መብቶች ክትትል መሰረት የትምህርትና የጤና አገልግሎት አቅርቦትን ጨምሮ በርካታ ጠንካራ ጎኖችን የተመለከተ ሲሆን፤ በአንጻሩ ክፍተቶችንም ለይቷል፡፡ በሁሉም የስደተኛ መጠለያ ጣብያዎች ውስጥ ሴቶች በወሊድ ወቅት እና በድኅረ ወሊድ በቂ የሕክምና አገልግሎት እንደማያገኙ፣ በመጠለያዎች ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርስ የጾታ ጥቃት መኖሩ፣ በአካባቢው ባለው የሥርዓተ-ጾታ ልማድ ምክንያት ማንኛውም ስራ ሴቶች ያለወንዶች ድጋፍ የሚያከናውኑ መሆኑን እና በቂ የንጽሕና መጠበቂያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በቂ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ተመልክቷል። ሴት ሕፃናት አብዛኛው ጊዜ በቤት ውስጥ ሥራ ስለሚጠመዱ ለትምህርታቸው ትኩረት እንደማይሰጡ፣ እድሜያቸው ከ6 ዓመት በላይ የሆኑ ሕፃናት አልሚ ምግብ ስለማያገኙ ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚጋለጡ ታይቷል፡፡ 

በተጨማሪም በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለአካል ጉዳተኛ እና አረጋዊያን ስደተኞች ተደራሽ አለመሆናቸው፣ በተለያዩ የተራድኦ ተቋማት የሚደረገው የአካል ጉዳተኞች መርጃ መሳሪያዎች ከስደተኞቹ ቁጥር ጋር አለመመጣጠን እና ልዩ ልዩ የአካል ጉዳት ላለባቸው የአካል ጉዳተኛ ስደተኛ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች (hearing aid and braille) አለመኖር ከተለዩት ክፍተቶች መካከል ናቸው።  እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መምህራን ስለአካል ጉዳተኝነት ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆን፣ የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ስደተኞች እንደየ አካል ጉዳታቸው የሚያስፈልጋቸው የትምህርት አሰጣጥ/ሥነ-ዘዴ አለመኖር፣ ለአካል ጉዳተኞች የመሰብሰቢያ እና የመዋያ ስፍራ (persons with disabilities friendly spaces) አለመኖር፣ ለአረጋዊያን የምገባ አገልግሎት አለመኖር፣ ለአረጋዊያን ድጋፍ የሚያደርጉ በቂ ድርጅቶች ባለመኖራቸው ምክንያት ለችግር መዳረጋቸውን መረዳት ተችሏል፡፡

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞች ፍላጎቶቻቸውን መሰረት ያደረገ እገዛ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ የማኅበረሰብ ክፍሎች በመደበኛ ሁኔታም ቢሆን ለአድሎ እና ጥቃት የተጋለጡ ሲሆን የስደተኝነት ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ ለጥቃት ያጋልጣቸዋል፡፡ ስደተኝነት ከፍ ላለ ብዝበዛ፣ መጎሳቆል እና መገለልን ጨምሮ ለጥበቃ ስጋቶች የሚያጋልጥ ከመሆኑ ባሻገር ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞች ሰብአዊ እርዳታን፣ ትምህርትን፣ ጤናን እና ሌሎች አገልግሎቶችን በእኩልነት ለማግኘት ይቸገራሉ። በተጨማሪም ለምሳሌ አረጋውያን ወይም አካል ጉዳት ያለባቸው በመሆናቸው ብቻ ለአድልዎ ይጋለጣሉ፡፡ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ከውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች እና የአመራር እድሎች ይገለላሉ። 

ስለሆነም፡

  • ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው የዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች እውቅና የተሰጣቸውን ‘የእኩልነት/equality’ እና የ‘ምክንያታዊ ማመቻቸት/reasonable accommodation’ መርሆችን ባገናዘበ መልኩ፣ መንግሥት በመንግሥት እና በተራድኦ ተቋማት ለስደተኞች የሚቀርቡ የሰብአዊ ድጋፎችም ሆኑ ሌሎች አገልግሎቶች ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ስደተኞች አካታች፣ ተደራሽ እና ሰብአዊ ክብራቸውን እና ደኅንነታቸውን በጠበቀ መልኩ መሆናቸውን ሊያረጋግጥ ይገባል፤
  • በተጨማሪም በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲሳተፉና ለመብቶቻቸው መከበር ሁኔታው ሊመቻችላቸው ይገባል፡፡
Location Ethiopia

Related posts

August 26, 2021February 12, 2023 Press Release
ምስራቅ ወለጋ፡ የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል
February 15, 2022August 28, 2023 EHRC Quote
ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የተወካዮች ም/ቤት ማፅደቁን ተከትሎ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ
September 29, 2022August 28, 2023 Event Update
A team of EHRC visited the South African Human Rights Commission (SAHRC) and other human rights institutions in South Africa
March 14, 2022March 14, 2022 EHRC on the News
Ambush and reprisals in Ethiopia kill 64 - rights body – Reuters

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on TwitterYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on Linkedin

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Women’s & Children’s Rights
    • HR Monitoring & Investigation
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter YouTube Linkedin Flicker
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.